SPHMMC
St Paul's Hospital Millennium Medical College
አስደሳች ዜና
የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ህ/ኮ ከሬድዮ ፋና የአንድ አመት የአየር ሰዓት በመግዛት የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ህ/ኮ የሚሰጣቸውን የህክምና አገልግሎቶች
ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም ስርጭት ለማዳመጥ  ከፈለጉ  ሁል ግዜ ማክሰኞ  ማታ ከ12፡30እስከ1፡00 በሬድዮ ፋና
ብሄራዊ ስርጭት በ6110 እና በ7210 kH 
Read more...
 
የደም ናሙና አቀዳድ ስልጠና ተሰጠ
የደም ናሙና ከታካሚዎች ለመቅዳት የራሱ የሆነ ልዩ ሳይንሳዊ ሂደቶች አሉት፡፡ በዚህም ምክንያት በአብዛኛው ጊዜ በተለይ ከህፃናትና ከጨቅላ ህፃናት የሚቀዱ ደሞች በትክክልና በአግባቡ ስለማይቀዱ ለታካሚዎች የማይጠቀሙ የተሳሳቱ የምርመራ  ውጤቶች እንዲሰጡ ከማድረጉም በላይ  ደሙ ለምርመራ ወደ ላብራቶሪ ከመጣም በኃላ ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህንና ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ የቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ህ/ኮሌጅ ከBD የሚባል ድርጅት ጋር በመተባበር ከተለያዩ የህክምና ክፍሎች ለተውጣጡ 30 ነርሶችና ለ10 የላብራቶሪ ባለሙያዎች የአንድ ቀን የቃልና የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
    በስልጠናውም ላይ አዳዲስ የደም ናሙና አቀዳድ ቴክኒኮች
Read more...
 
የዓለም የጉበት በሽታ ቀን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተከበረ የጉበት በሽታ መድኃኒት በኢትዮጵያ መመረት ጀምሯል
የዓለም የጉበት በሽታ ቀን በኢትዮጵያ ተከበረ፡፡ የቀኑ መከበርም ለህብረተሰቡ በበሽታው ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግና በበሽታው የሚሰቃዩ ሰዎችን ለማዳን፣እንዲያገግሙ ለማድረግና የቅድመ መከላከል ስራን በስፋት ለመስራት እንዲቻል መሆኑ ተገልÛል፡፡ ‹‹ የጉበት በሽታን ለማከም የሚያስችል መድኃኒትም በኢትዮጵያ መመረቱም ተሰምቷል››፡፡
 በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የዓለም የጉበት በሽታ ቀን በተከበረበት ወቅት የኢትዮጵያ ጋስትሮ ኢንትሮሎጂ ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃኔ ረዳኢ እንደተናገሩት፤ዓለም አቀፍ የጤና ማህበር ከሚያከብራቸው አምስት ዓለም አቀፍ ቀኖች ውስጥ የጉበት በሽታ ቀን አንዱ ነው፡፡ የቀኑ መከበርም በዓለም አቀፍም ሆነ በአገር ደረጃ በሽታው ከዕለት እለት እየጨመረ በመምጣቱ መፍትሄዎችን ለማፈላለግና ችግሮቹ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ለመስራት ያስችላል፡፡
Read more...
 
የተቀናጀ የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና መኮንኖች ተመረቁ
  ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ  በተቀናጀ  የድንገተኛ ቀዶ ሕክምና መኮንንነት ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 12 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ በኮሌጁ የሚሰጡ የድህረ ምረቃ ትምህርቶችም በሚቀጥለው ዓመት 23 ለማድረስ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
    የምረቃ ሥነ ሥርዓቱን በሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ትንንት በተካሄደበት ወቅት የኮሌጁ ምክትል ፕሮቮስት ዶክተር ውለታው ጫኔ እንደተለፁት፤ ኮሌጁ ያስመረቃቸው እነዚህ ተማሪዎች ላለፉት ሶስት ዓመታት የንድፈ ሃሳቡና የተግባር ትምህርታቸውን በተቋሙ ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ብለዋል፡፡
Read more...
 
ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን የአልባሳትና የተለያዩ ቁሳቁሶች እርዳታ ተደረገ፡፡
መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ ራሳቸውን ችለው መፀዳዳት፣መመገብና መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ800 በላይ የሚሆኑ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ከወደቁበት ጉዳና ላይ በማንሳትና ቤተሰባዊ ፍቅር በመስጠት ተገቢውን እንክብካቤ እያደረገ ይገኛል፡፡
     ይህን  በመገንዘብ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል የወጥቤት እቃዎች ፣አልባሳቶችንና አልጋዎችን ለማዕከሉ በስጦታ አበርክቷል፡፡
Read more...
 
«StartPrev1234567NextEnd»

Page 1 of 7
 

User login

Use your SPHMMC loginSPHMMC

  • Medical Education
  • Capacity development of human resource(CME training, scholarship, pedagogic training, recruitment of instructors )   
  • Continues revision of integrated medical curriculum
  • Increasing area of training(post graduate and specialty program)
  • Producing up-to-date research(problem solving ,community based)
  • Partnership (other medical university ,  donors  )