ማስታወቂያ

ማስታወቂያ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2009 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በሕክምና ትምህርት አዲስ ተማሪዎችን ለማስተማር ባወጣው ማስታወቂያ ተወዳድራችሁ ኮሌጃችን ለተቀበላችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ

የምዝገባ ወቅት ጥቅምት 8፣9 እና 10/2009 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ለምዝገባ በምትመጡበት ጊዜ

  • የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውንና ኮፒ
  • የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒ
  • ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪኘት ዋናውና ኮፒ
  • 3 በ 4 የሆነ ስምንት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
  • የግል መጠቀሚያችሁን ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ ይዛችሁ በመምጣት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ

ኮሌጁ ከተጠቀሰው ጊዜ በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን አያስተናግድም

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ