የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለ2009…

STUDREGየቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ያስታውቃል፡፡

 

የመግቢያ መስፈርት

 1. በ2008 ዓ.ም የአገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው
 • ለአዳጊ ክልሎች /ለጋምቤላ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ቦረና ዞንና ዋግምራ ዞን/

ለወንዶች 451 እና ከዚያ በላይ

ለሴቶች 426 እና ከዚያ በላይ ያመጡ

 • ለሌሎች ክልሎች

ለወንዶች 526 እና ከዚያ በላይ

ለሴቶች 501 እና ከዚያ በላይ

 1. የማመልከቻ ጊዜና ቦታ
 • ከነሐሴ 22 እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2008 ቅዳሜን ጨምሮ በኮሌጁ ሬጅስትራር ቢሮ እና በክልል ጤና ቢሮዎች
 1. ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ
 • ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
 • የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤቶች ኦርጅናልና ኮፒ
 • ከ9-12 ትራንስክሪኘት ኦርጅናልና ኮፒ
 • የመመዝገቢያ ክፍያ 50 ብር
 1. የመግቢያ ጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ
 • ጳጉሜ 1/2008 ዓ.ም በመድሃኔአለም መሰናዶ ት/ቤት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት
 • የቃል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ጳጉሜ 3-4/2008 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃ ከድህረ ገፃችን www.sphmmc.edu.et መመልከት ይችላሉ