ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም (MSc, MPH and PhD) ለመማር ተመዝግባችሁ GAT ያልወሰዳችሁም ሆነ ተፈትናችሁ የGAT የማለፊያ ውጤታችሁያልተሟ ላለችሁ እና እንደአዲስ ማመልከት ለምትፈልጉ በሙሉ፡፡
- ከዚህ ቀደም የGAT ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላችሁ እና ከዚህ ቢፊት ለኮሌጃችን ያላመለከታችሁ፤
- ከዚህ ቀደም ያልተፈተናችሁና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያላገኛችሁ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት የመመዝገቢያ ቀን November 6-10/2023 ቀን ሲሆን የመፈተኛ ቀን November 13-17/2023 በመሆኑ ፈተናውን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- ለበለጠ መረጃ እና ለፈተናው ለመመዝገብ የአዲስ አበባዩ ኒቨርስቲ የመረጃ መረብን (https://portal.aau.edu.et) መመልከት ትችላላችሁ፡፡
ስለዚህ የማለፊያ ውጤት ያላችሁም ሆነበተራ ቀጥር 2. በተገጸው መሰረት ፈተናውን ወሰዳችሁ የማለፊያ ውጤት የምታስመዘግቡ በሙሉ በኮሌጃችን ሬጅስትራር በመቅረብ ከ November 20-24/2023 ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳውቃልን፡፡